ነሐሴ 20 ፣ 2013

ለታላቁ የህዳሴ ግድብና ለኢትዮጵያ የብዝኃ ህይወት ስጋት የሆነው እምቦጭ

City: Bahir Darአካባቢወቅታዊ ጉዳዮች

በኢትዮጵያ ወደ 35 የሚጠጉ ጎጂ እፅዋት ተመዝግበው ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የእንቦጭ አረም ነው። በፈጣን ደረጃ የመባዛት፣ የመስፋፋት፣ ራሱን የመተካት እና የመቋቋም ኃይል ያለው በመሆኑ ምቹ ሁኔታን ሲያገኝ በ5 ቀናት ውስጥ...

Avatar: Ayele Addis
አየለ አዲስ

Ayele Addis is an award winner Journalist, Journalism, Trainer, Researcher, and Media & Communication Development Consultancy for Thomson Reuters' Foundation, Africa News Channel, Amhara Media, and Journalists Association. Ethiopian Mass Media Action (EMMA News), ARMA Media Production.Woldia University and Bahir Dar University and founder of Journal of Ethiopian Media and Communications.

ለታላቁ የህዳሴ ግድብና ለኢትዮጵያ የብዝኃ ህይወት ስጋት የሆነው እምቦጭ

በኢትዮጵያ ወደ 35 የሚጠጉ ጎጂ እፅዋት ተመዝግበው ይገኛሉ፡፡ በአካባቢያዊ ስነ- ምህዳር፣ በእርሻ፣ በግጦሽ መሬት፣ በፓርክ፣ በሀይቆችና ወንዞች፣ በኃይል ማመንጫ ግድቦችና በመስኖ ውሃ ማስተላለፊያዎች፣ በኢኮኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቀሰሴዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ የእንቦጭ አረም ነው፡፡ እምቦጭ ሰፋፊ አረንጓዴ ቅጠሎችና የወይን ጠጅ አበባዎች ያሉት ሲሆን የውሃ ላይ ተንሳፋፊ አረም ነው፡፡ በሐይቆች እና በወንዝ ዳርቻዎች በተለያየ የርዝመት መጠን ቢለያይም እስከ 1 ሜትር በውሃ ላይ እና እስከ 80 ሴ.ሜ. ከውሃ በታች ማደግ ይችላል፡፡    

በፈጣን ደረጃ የመባዛት፣ የመስፋፋት (ራሱን የመተካት) እና የመቋቋም ኃይል ያለው በመሆኑ ምቹ ሁኔታን ሲያገኝ በ5 ቀናት ውስጥ ራሱን በሁለት እጥፍ የማባዛት አቅም አለው፡፡ ፍሬውም በአፈር ውስጥ እስከ 20 ዓመት የመቆየት ብቃት አለው፡፡

ካልተነገሩት የእንቦጭ የብዝኃ ሕይወት ፈተናዎች ውስጥ በባህር አሳ ምርት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ አንዱ ነው፡፡ በጣና ሐይቅ የባህር አሳን ምርታማነት በእጅጉ እየቀነሰ ይገኛል፡፡ ሐይቁ ላይም የባህር ትራንስፖርት ጉዞን ገትቷል፡፡ አርሶ አደሮችን ከማሳቸው እያፈናቀለ፣ ውሃማውን መሬት ወደ ደለል ቀይሯል፡፡  

የጣና ሃይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃ እና ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አያሌው ወንዴ እንቦጭ ወደ ሕዳሴ ግድብ ሔዷል ይላሉ። በኃይል ማመንጫው ላይም ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡ በ2013 ዓ.ም. የጣና ሀይቅን በሰው ኃይልና በማሽን በመታገዝ ከእንቦጭ አረም ለማፅዳት ጥረት ቢደግም 43 ሺህ ሄክታር የውኃው አካል በእምቦጭ አረም ተወሯል፡፡ ይህንንም ግዙፍ ውሃማ አካል ወደ የብስነት ለመቀየር ስጋት ደቅኗል፡፡ ምርታማነት ቀንሷል፡፡

ዶ/ር አያሌው በዘርፉ ባደረጉት ምርምርና በሚመሩት የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃ እና ልማት ኤጀንሲ ስራውን በቅርበት እንደሚመራ የስራ ባለሙያ እና ኃላፊ “የእንቦጭ አረም በጣና ሀይቅ ዙሪያ የሚገኙ ነባር የውሃ አዘል እጽዋትን በማጥፋቱ ምክንያት የቆሮሶና ሌሎች የዓሳ ዝርያዎች የመራቢያ ስፍራ በደለል የሚሞላ በመሆኑ በዓሳ ሀብቱ ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነው” ብለዋል፡፡  

እንቦጭ የፀሐይ ብርሃንን በመከልከል Photosynthesis እንዳካሄድ በማድረግ እድገቱን በመግታት ዓሳዎች ምግብ እንዳያገኙ  ተፅእኖ በመፍጠሩ፣ እንዲሁም ቆሮሶ እየተባለ የሚጠራው የዓሳ ዝርያ በቂ ኦክስጅን ካላገኝ የማይራባ በመሆኑ በቂ ኦክሲጂን እንዳያገኝ በማድረግ ዓሳውን እንደሚገድለው የኢትዮጵያ የዓሳና የውሃ ሳይንስ ባለሞያዎች ማህበር ይገልፃሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2017 Spring International Publishing በተሰኘ ተቋም በአቶ ጎራው ጎሹና ሽመልስ አያሌ በተዘጋጀው Problem overview of the lack tana basin  በሚል ርዕስ ባሳተሙት የምርምር ስራ ፣ የእንቦጭ አረም ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት የሚያስችል ስትራቴጂ ባለመነደፉ የጣናን ሀይቅ በአጭር ግዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በአረሙ የሚሸፈን ስለሆነ የአሳ ኢንዱስትሪውንና የትራንስፓርት አገልግሎትን እያዛባ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በውሃው ውስጥ ብዝሀ ህይወት ከማዛባት ባሻገር የውሃ ትራንስፖርትንና ሚሊዮኖች በሚተዳደሩበት የዓሣ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን፣ አረሙ የአስጋሪዎችን መረብ በቁርጥራጩ አይኑን በመዝጋት ዓሣ እንዳይዝ ከማድረጉም በተጨማሪ መረቡን ከአረሙ ለማላቀቅ የሚወስድባቸዉ ሰዓት ግማሽ ቀን መሆኑን ከባህር ዳር ዓሣና ሌሎች የዉሃ ዉስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክትር አቶ ደረጄ ተዋበ የእንቦጭ አረም በጣና ሀይቅ ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅእኖ አስመልክተው አስታውቀዋል፡፡

እ.አ.አ. በ2017 በ Net Journal of Agricultural Science ተቋም  Vol. 5(1), pp. 8-15 በታተመው ጆርናል በጣና ሀይቅ ላይ የእንቦጭ አረም በመስፋፋቱ የአሳ ማጥመድ ስራን እያስተጓጎለ በመሆኑ በሀይቁ አካባቢ በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ ከፍተኛ ችግር ፍጥሯል ሲል በምርምሩ አስፍሯል፡፡

በጣና ሐይቅ ብዝኃ ሕይዎት ዙሪያ ምርምር ያደረጉት አቶ አስማረ አርኪ በበኩላቸው በጣና ሀይቅ ላይ በሰሜን ምስራቅ የሀይቁ አካባቢዎች የእንቦጭ አረም በመስፋፋቱ የዓሳ ምርት እየተዳከመ መምጣቱን ከአሳ አስጋሪዎች መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማራመሪ የሆኑት ዶ/ር አያሌው የእንቦጭ አረም በክረምት ወራት በሜዳማው የጣና ሀይቅ አካባቢ (ደንቢያና ፎገራ) በመሰራጨቱ በሺዎች ሄክታር የሚሆን የውሃ አዘል፤ ግጦሽና የእርሻ መሬት ከጥቅም ውጪ አድርጓል ብለዋል፡፡

የሳቸውን ሃሳብ የሚደግፈው በ2017 እአአ Net Journal of Agricultural Science  ተቋም Vol. 5(1), pp. 8-15  በታተመ የምርምር ስራ በጣና ሀይቅ ዙሪያና ርጥበታማ ቦታዎች ላይ ለከብት መኖ የሚያገለግል በርካታ ሀገር በቀል የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ሳሮች ቢገኙም የእንቦጭ አረም በሀይቁና በረግረጋማ ቦታዎች ላይ በመስፋፋቱ ለከብቶች መኖ የሚውሉ ሳሮችን በመሻማት እያጠፋ የሚገኝ በመሆኑ በከብቶች መኖ እና ምርት ላይ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን አረጋግጠዋል፡፡

አቶ አስማረ እርኪ በተጨማሪም የእንቦጭ አረም በዝናብ ወቅት በጎርፍና በማዕበል ከጣና ሀይቅ ላይ በመገፋት ወደ እርሻ መሬቶችና ረግረጋማ ቦታዎች በመሄድ የእርሻ ቦታውን በአረሙ ሰለሚሸፈን አርሶ አደሩ ለእሩዝ እርሻ የሚገለገልበትን መሬት እያስለቀቀው ነው ብለዋል፡፡ በተለይም አረሙ ረጃጅም ስሮችና ሰፋፊ ቅጠሎች ባህሪ ምክንያት መሬቱን በመቆንጠጥና በመጠቅጠቅ የሚይዝ ስለሆነ የእርሻ መሬቱን ለማረስ አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ አረሙን ለማስወገድ ተጨማሪ የሰው ሀይል እንዲያወጡ እያስገደዳቸው መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡

የእንቦጭ አረም በጣና ሀይቅ ዙርያ ባሉ አርሶ አደሩ በሩዝ ማሳቸዉ ላይ በማዕበል አማካኝነት ዘልቆ በመግባት እሩዙን ወደዉስጥ በመቅበር እንዲሞት እያደረገ እንደሚገኝ እና የጣና የዉሀ መጠን በሚቀንስበት ወቅት አርሶ አደሩ መሬቱን በቀሪዉ እርጥበታማ መሬት ወይም መስኖ በመጠቀም ለማምረት ሲሞክር መሬት የያዘዉን የእንቦጭ አረም ለማጽዳት ብዙ ጉልበት እየጠየቀ እንደሚገኝ ከባህር ዳር ዓሣና ሌሎች የዉሃ ዉስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክትር አቶ ደረጄ ተዋበ ገልፀዋል፡፡

እንቦጭ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት ገባ

አንድ አይነት ወጥ መረጃ ለማግኝት ቢቸግርም የእንቦጭ አረም በ1950 በአባ ሳሙኤል ግድብ አካባቢ የታየ መሆኑንና አገባቡም አካባቢን ከማስዋብ አንጻር መሆኑ የሚነገር ሲሆን፣ አረሙ ከግዜ ወደ ጊዜ አካባቢዉን እንዳዳረሰና በአዋሽ ወንዝ አማካኝነትና በሌሎች ዘርፈብዙ ምክንያቶች በ1956 ዓ.ም በቆቃ ሀይቅ እና በአዋሽ ወንዝ ላይ ታይቷል ሲሉ አጥኝዎች ይገልፃሉ፡፡ በ1965 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አደገኛ አረም በመባል  እውቅና  የተሰጠው ሲሆን  በሌላ ጥናት የእንቦጭ አረም በ1965 ዓ.ም በላይኛው አባይ ተፋሰስ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የሚገመት ሲሆን፣ ላለፉት አራት አሥርት ዓመታት በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ሐይቆችና ወንዞች ላይ በፍጥነት በመዛመትና በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

እንቦጭ አረም በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ በጣና ሐይቅና በጢስ አባይ ወንዝ ዙሪያ፣ በስምጥ ሸለቆ አካባቢ በአዋሽ ወንዝ፣ በኢሉ-አባቦራ ዝቅተኛ ቦታዎች በሚገኙት የባሮ፣ ጊሎ እና ፒቦር ወንዞች፣ በዝዋይ ሐይቅ እና በቆቃ ግድብ ላይ በስፋት በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡በአማራ ክልላዊ መንግስት በጣና ሀይቅ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቆቃ ግድብና በዝዋይ ሀይቅ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት በአባያና ጫሞ ሀይቆች ላይ ተንሰራፍቷል፡፡

የእንቦጭ አረም ዘሩ ለረጅም ጊዜ ሳይሞት  መቆየት በመቻሉ በሀይቆችና ወንዞች ላይ በመንሰራፋት የሚያሳድረው ጉዳት ከፍተኛ ሲሆን ከእነዚህም በጥቂቱ ብዝሀ ሕይወትን ማመናመንና ማጥፋት፣ የዓሣ ምርትና ምርታማነትን መቀነስ፣ የምግብ ዑደትን ማዛባት፣ የመስኖ ልማትን ማደናቀፍ፣ የቱሪዝም ዕድገትን መቀነስ፣ የውኃ ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስተጓጎል፣ በውኃ አጠቃቀምና አቅርቦት ላይ ችግር መፍጠር፣ የውኃ-ወለድ በሽታ አምጭ ተዋህሲያን መራቢያ መሆን፣ የውኃ ትነትንና ብክነትን መጨመር፣ የተወረሩ የውኃ ሥርዓተ-ምህዳሮችን ወደ ውኃ አዘል መሬት መለወጥ፣ በውኃ ውስጥ የሚገኘውን የኦክስጂን መጠን በመቀነስ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀዉስ እያደረሰ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት የጣና ሀይቅ 43 ሺህ ሄክታር የውኃው አካል በእምቦጭ አረም ተወርሮ ጣናን ወደ የብስነት ለመቀየር ስጋት ደቅኗል፡፡

የመስፋፋቱ መንስኤ

ለዚህ ሁሉ ሰፊ መስፋፋት እንደምክንያትነት የሚጥቅሱት ተመራማሪዎች እ.አ.አ በ2017 Springer International Publishing ተቋም በአቶ ጎራው ጎሹና ሽመልስ አያሌው በታተመው (Problem overview of the lake tana basin) የምርምር ጥናት የእንቦጭ አረም ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት የሚያስችል ስትራቴጂ ባለመነደፉ አረሙ የጣናን ሀይቅ በአጭር ግዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመሸፈን በአጠቃላይ የአካባቢውን ስርዓተ ምህዳር እያዛባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እ.አ.አ በ2017 ( Net Journal of Agricultural Science) ተቋም  የባህርዳር ዓሳና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ተቋም ባሳተመው ጆርናል ህብረተሰብን በማሳተፍ የእንቦጭ አረም ለመንቀል ከሚደረገው ሙከራ በስተቀር አረሙን ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት የሚያስችል ምንም ዓይነት ስትራቴጂ ያልተነደፈ መሆኑ አብራርቷል፡፡

የእንቦጭ አረም ፈጣን የመባዛት ስነ ህይዎታዊ ባህሪይ ጋር እኩል መራመድ የሚችል የማስወገጃ ስልት ጥቅም ላይ ማዋል አለመቻሉን ከአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዓመታዊ ሪፖርት ከተከለሱ ማስረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡

በጣና ሀይቅ ላይ በህብረተሰብ ተሳትፎ የእንምቦጭ አረምን ለማስወገድ ጥረት ቢደረግም በሀይቁ ውስጥ በሚገኙ ቢላሀርዚያ (health threats of bilharzias)፣ አልቅት (leech bites)፣ የወባ በሽታ (malaria)  እና የውሃው ቅዝቃዜ (cold water environment) ምክንያት ለስራው እንቅፋት በመሆኑ በተፈለገው መጠን መቀነስ እንዳልተቻለ ታውቋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በእንቦጭ መስፋፋት ዙሪያ የስራ ሀላፊዎች ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ  በጣና ሀይቅ ላይ የእንቦጭ አረም የስርጭት መጠኑን መቆጣጠር ባለመቻሉ ከጣና ሀይቅ ባለፈ በአባይ ወንዝ ላይ አረሙ በመገኘቱ ወደፊት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ከፍተኛ ስጋት በመፈጠሩ ዩኒቨርስቲው በሰው ሀይል በመጠቀም አረሙን የማስወገድ ስራ እየሰራ መሆኑ ገልጸዋል፡፡

የእንቦጭ አረም መኖሪያዉን ከባህር ዳር ዩኒቨረስቲ ፔዳ ግቢ ጀርባ የአባይ ወንዝን ተገን ካደረገ አመታት ማስቆጠሩን እና የህዳሴ ግድብን የመዉረር ዕድሉ ከፍ ያለ መሆኑን የባህር ዳር የውሃና ሌሎች የውሃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል የእንቦጭ አረምን አስመልክቶ ያወጣው ሰነድ ያሳያል፡፡

አረሙን ለማጥፋት በጣና ሐይቅ የተከናወኑ ተሞክሮዎች

በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ለመቀነስ የአማራ ክልላዊ መንግስት አካባቢ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን፣ የባህር ዳር እና የጎንደር ዩኒቨርስቲ በራሳቸው ተነሳሽነት የተለያዩ የማጥፊያ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል፡፡ ጣናን የወረረውን እምቦጭ አረም  በተባበረ ሀገራዊ ክንድ ለማስወገድ የሚያስችል ለአንድ ወር የሚዘልቅ ዘመቻ ጥቅምት ዘጠኝ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፈንታ ማንደፎሮ (ዶ/ር) “ጣናን ከህመሙ የመታደጉ ተግባር የተቀናጀ ባለመሆኑና ወደ  ሀገር አቀፍ ደረጃ ባለማደጉ ችግሩን መፍታትና ዘላቂ መፍትሄ ማበጀት ሳይቻል ቀርቷል፤ አሁን ግን የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመምከር አጀንዳው ሀገራዊ እንዲሆን ተደረጓል” ሲሉ ገልጸዋል:: 

የአማራ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም በፊዚካል የማጥፊያ ዘዴ እስከ ወረዳ ድረስ ያለውን ህብረተሰብ በማስተባበር በከፍተኛ ንቅናቄ በእጅ የመንቀል ስራ ሰርቷል፡፡ እንዲሁም በመካኒካል የማጥፊያ ዘዴ ከአማጋ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ 52,000 ዶላር ተገዝቶ በእርዳታ ለባለስልጣኑ በተለገሰው የእንቦጭ አረም ማጨጃ ማሽን አረሙን ከጣና ሀይቅ ላይ እያስወገደ የሚገኝ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ማጨጃ ማሽኑ አረሙን ለማጨድ የሚያስችለው ሸክላ በመሰበሩ ምክንያት ማሽኑ ያለ አገልግሎት በጣና ሀይቅ ላይ አቁሟል፡፡

የእንቦጭ አረምን ለማጨድ በአማጋ ኃ/የ/የግል ማህበር በስጦታ የተለገሰ ማሽን (Photo)

የአማራ ክልል አከባቢ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከአለም አቀፍ የጣና ደህንነት ህብረት (ዲያስፖራ) ከካናዳ ተገዝቶ በእርዳታ ለባለስልጣኑ የተሰጠው ማጨጃ ማሽን ቢኖርም በጣና ሀይቅ ላይ ያለው የእንቦጭ አረም ብዛት ያለው እና የተጠቀጠቀ በመሆኑ ማሽኑ አረሙን የማጨድ አቅሙ አነስተኛ በመሆኑ ማሽኑ ያለ አገልግሎት ጣና ሀይቅ ላይ ቆሙ እንደቀረ የስራ ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የእንቦጭ አረምን በሜካኒካል የማጥፊያ ዘዴ ለማስወገድ እንዲቻል በ19 ሚሊየን ብር የእንቦጭ አረም ማጨጃ ማሽን እና የታጨደውን አረም ወደዳር ለማውጣት የሚያስችል 30 ሜትር የሞተር ጀልባ ከሙላት ኢንጂነሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር በጋራ በመሆን ዲዛይን በማድረግ በማሰራት ላይ ይገኛል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሙላት ኢኒጂነሪንግ  በ19 ሚሊዮን ብር እያሰራ ያለው የእንቦጭ ማጨጃ (Photo)

በተጨማሪም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ግቢ በባይሎጂካል የእንቦጭ አረምን የማጥፊያ ዘዴ ደግሞ 150 የእንቦጭ አረምን የሚመገቡ ጢንዚዛዎችን ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ በማስመጣት በላብራቶሪ እያባዛ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል፡፡

 

 በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ግቢ የእንቦጭ አረምን የሚመገቡ ጢንዚዛዎች በባዮሎጂካል ዘዴ (Photo)
 በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ግቢ የእንቦጭ አረምን የሚመገቡ ጢንዚዛዎች በባዮሎጂካል ዘዴ (Photo)
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ 1.8 ሚሊዮን ብር ወጪ ተሰርቶ ያለአገልግሎት ጎርጎራ ወደብ ላይ ቁሞ ይገኛል (Photo)

በተጨማሪ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ለማጥፋት በባይሎጂካል የማጥፊያ ዘዴ ከኢትዮጵያ ደን ምርምር ኢንሲቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን በሙከራ ደረጃ ፈንገስ በማራባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ምርምሩ ከላብራቶሪ ወደ pond (ኩሬ) ማደጉን፣ እንዲሁም ከወሎ ዩኒቨርስቲ በጋራ በመሆን በጣና ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም በኬሚካል ዘዴ ለመቆጣጠር እንዲቻል ሲትሪክ አሲድ ከእስራኤል ሀገር በማስመጣት በሙከራ ደረጃ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን የሚመለከታቸው የሥራ ሃላፊዎች በቀረበላቸው ቃለ-መጠይቅ ገልፀዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንቦጭ አረምን በባይሎጂካል ዘዴ ለመቆጣጠር የፈንገስ የpond (ኩሬ)(Photo)

 

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንቦጭ አረምን በባይሎጂካል ዘዴ ለመቆጣጠር የፈንገስ የpond (ኩሬ)(Photo)

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንቦጭ አረምን በባይሎጂካል ዘዴ ለመቆጣጠር የፈንገስ የpond (ኩሬ)(Photo)

አስተያየት