መጋቢት 26 ፣ 2015

ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለዓለም አቀፍ የአይሲቲ የፍፃሜ ውድድር አለፉ

City: Addis Ababaቴክ

በዘንድሮው የሁዋዌ ግሎባል አይሲቲ የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በሚደረገው ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ለዓለም አቀፍ የአይሲቲ የፍፃሜ ውድድር አለፉ

ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ተመዝግበው በበይነ መረብ አማካይነት ፈተና የወሰዱ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ፈተናውን ማለፍ የቻሉ 63 ተማሪዎች በብሔራዊ የአይሲቲ ውድድር ላይ ሲሳተፉ ቆይተዋል። 

በተያዘው 2015 ዓ.ም. ታህሳስ ወር በአዲስ አበባ ሁዋዌ እና የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በመተባበር በተካሄደው ውድድር በድምሩ 15 የሚያልፉ ተማሪዎች ተለይተው ቀጣይ ዙር ውድድር ላይ ቆይተዋል።

ስድስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ወደ ዓለም አቀፉ የሁዋዌ ኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) የፍፃሜ ውድድር ማለፋቸውን የሁዋዌ ኩባንያ የኢትዮጵያ ቢሮ ለአዲስ ዘይቤ በላከው መግለጫ አስታውቋል። ተማሪዎቹ በቻይና በሚካሄደው የሁዋዌ አይሲቲ የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉም ይጠበቃል።

የሁዋዌ ኢትዮጵያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሊሚንግ ዪ በውድድሩ የተሳተፉ ተማሪዎችን አመስግነው የሁዋዌ የአይሲቲ ውድድር በዓለም ዙሪያ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአይሲቲ ዘርፍ ውድድር እያደረጉ ሃሳባቸውን እንዲለዋወጡ ያስቻለ መድረክ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2015 ጀምሮ የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ ውጤቶቹ ያመላክታሉ። እ.ኤ.አ በ2022 በተደረገው የአይሲቲ ውድድር ላይ ከ85 የተለያዩ ሀገራት 150 ሺህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን ገልፀው ነበር።

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በውድድሩ መሳተፍ ከጀምሩ አራተኛ ዓመቱን ይዟል።

አስተያየት