ጥቅምት 2 ፣ 2014

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ24 የዓለም ደሃ ሀገራት የዕዳ እፎይታ ዉሳኔ አጸደቀ

City: Addis Ababaዜና

የገንዘብ ድጋፉ ሀገራቱ የኮሮና ወረርሽኝ ያስከተለባቸውን ተጽዕኖ መቋቋም እንዲችሉ ታስቦ መሆኑን ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

Avatar: Solomon Yimer
ሰለሞን ይመር

Solomon is a content editor at Addis Zeybe. He has worked in print and web journalism for six years.

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ24 የዓለም ደሃ ሀገራት የዕዳ እፎይታ ዉሳኔ አጸደቀ

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ24 የዓለም ደሃ ሀገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ። የገንዘብ ድጋፉ ሀገራቱ የኮሮና ወረርሽኝ ያስከተለባቸውን ተጽዕኖ መቋቋም እንዲችሉ ታስቦ መሆኑን ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

የብድር እፎይታ ፕሮግራሙን እስከ ጥር 10 ቀን 2022 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ፕሮግራሙ 124 ሚሊየን ዶላር እንደሚሆን አይ ኤም ኤፍ በመግለጫው አስታውቋል።

ተጨማሪ 116 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ከጥር አጋማሽ እስከ ሚያዝያ አጋማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ለሀገራቱ ይለቀቃል ሲልም ተቋሙ አስታውቋል። 

ይህ የብድር እፎይታ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የፈጠረዉን የጤና ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቋቋም ሀገራቱ ለሚወስዱት እርምጃ የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥማቸዉ ለማድረግ ያግዛል ሲል አይ ኤም ኤፍ በመግለጫው አስታውቋል።

በእፎይታ ፕሮግራሙ ከሚካተቱ ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡርኪና ፋሶን ፣ ቻድን ማሊን ፣ የመን ፣ የሶሎሞን ደሴቶች እና ታጃኪስታን ይኙበታል።

በመጋቢት 2020 የኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ አይ ኤም ኤፍ ለደሀ ሀገራት የዕዳ እፎይታ ለመስጠት 1.4 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለማሰባሰብ የጀመረ ሲሆን እስካሁን ብሪታኒያ ፣ ጃፓን ፣ ጀርመን እና ሌሎች የአውሮፓ እና የእስያ አገሮችን ለዚሁ ተግባር የሚዉል 860 ሚሊዮን ዶላር ያህል ቃል ገብተዋል።

በሌላ በኩል ባሳለፍነዉ ሰኔ ኢትዮጵያ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ዕዳ አከፋፈል ማስተካከያ ለማድረግ በድርድር ላይ እንደምትገኝ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በቡድን 20 የጋራ የብድር ማዕቀፍ ስር ያሉባት ብድሮች እንዲራዘሙላት ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር የጠየቀችውን ጥያቄ አስመልክቶ የብድር ሰጪ ሃገራት ኮሚቴ መስከረም 06፣ 2014 ዓ.ም ለመጀመርያ ጊዜ ስብሰባ በመቀመጥ አዎንታዊ ምላሽ ማሳየቱን የገንዘብ ሚኒስቴር ማስታውቁ ይታወሳል። ይኸ ለኢትዮጵያ እስከ ስድስት አመታት የመክፈያ ጊዜ እፎይታ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

አስተያየት