በጮቄ ተራራዎች እና ተክሎች መሀል በወጣቱ አብይ አለም የተመሰረተው 'ሙሉ ኢኮሎጅ መንደር' የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ሆኖ ተመረጧል
ድምጻዊ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) “የትዝታው ፈረስ” በተሰኘው ሙዚቃው ውስጥ እንዲህ ሲል አዚሟል፥ “የሳር ተራው ሲሳይ ያስመሸኝ ካራዳ፣ የድሃ እራት ንፍሮ የብርቅዬ ጓዳ”
ልጅ ሆኜ የቆሎ ተማሪ እያለሁ እርሳቸው የሚተክሉትን ችግኝ ከወንዝ ውሃ እያመጣን በማጠጣት እናግዛቸው ነበር። ተግባሩን ልማድ አድርጌው አሁን ድረስ ችግኝ እተክላለሁ ~መሪጌታ እዝራ በአምላኩ
በአትጠገብ እልፍኝ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች መግባት አይችሉም፣ የጦር መሳሪያ ይዞ መግባት አይቻልም፣ ዘመናዊ መጠጫ ወይም መመገቢያ ወደ ቤቱ አይገባም
የወይባ ጭስ በወሊድ ውቅት ማህፀን አካባቢ የሚፈጠር ቁስለት ቶሎ እንዲደርቅና እንዲድን ከማድረጉ ባሻገር ለመልካም ጠረንና ለሰውነት ጥራት እንደሚጠቅም በማህበረሰቡ ይታመናል
በዓላትን ተከትሎ በትልልቅ ከተሞች ኤግዝቢሽንና ባዛሮች የተለመዱ ሲሆን በአነስተኛ ከተሞች ደግሞ ተጓዥ ባዛሮች በስፋት ይታወቃሉ
“ኦርካም ማይ አይ” የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደራሽነታቸው ዝቅተኛ ለሆኑ እንዲሁም በትምህርትና በእለት ተለት ህይወታቸው አያሌ ተግዳሮት ላለባቸው ኢትዮጵያዊ አይነ ስውራን የተስፋ ብርሃን ፈንጥቋል
የሱዙኪ ዲዛየር መኪኖች ከዋጋቸው በተጨማሪ ነዳጅ ቆጣቢ በመሆናቸው እንዲሁም ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ አለመሆናቸው ተመራጭ ካደረጓቸው ሁኔታዎች ተጠቃሾቹ ናቸው
የአሸንዳ በዓል በመቀሌ ከተማ በፌስቲቫል ደረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በተገኙበት ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይከበራል
በትግራይ አሸንዳ፣ በሰቆጣ ሻደይ፣ በላሊበላ አሸንድዬ፣ በቆቦ ሶለል እየተባለ ቢጠራም የጋራ ትርጉሙ ለምለም ማለት እንደሆነ ይነገራል።