በደሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ 88 ኢንተርፕራይዞች የወሰዱትን የተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር መክፈል አልቻሉም።
ዉሽዉሽ ሻይ ልማት ድርጅት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል አረንጓዴ ሻይ ቅጠል በኪ.ግ በ4.92 ብር እንዲሁም ለውጭ ገበያ ደግሞ በ7.38 ብር ከአርሶ አደሮቹ ላይ ይረከባል።
የጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ወንድሙ አዲስ ከአዲስ ዘይቤ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዘንድሮው 2014 ዓ.ም 11 ሚሊዬን 613 ሺ 144 ብር የሚያወጣ የኮንትሮባንድ እቃ መያዛቸውን ነግረውናል።
በሃይቁ በቀን ብቻ ሳይሆን በለሊትም በዓሳ ማስገር ስራ የተሰማሩ ሰዎች ሲኖሩ የቀናቸው ከ200-300 ዓሳ፤ ያልቀናቸው ባዶ እጃቸውን የሚመለሱም አሉ
አንድ ሰው ገቢው እያነሰ ፍላጎቱ ደግሞ እየጨመረ ሲሄድ ጭንቀቶቹን ለመርሳት ከሚጠቀማቸው ተግባራት መካከል ያለውን ትንሽ ገንዘብ ለጊዜያዊ ደስታ ማባከን እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ
አርሶ አደሮቹ በማሳቸው ላይ የሚገኘውን ተክል የረዥም ጊዜ ጉዳት ከተረዱ በኋላ ማሳቸውን ጠቃሚ ወደ ሆኑ የፍራፍሬ ምርቶች እየቀየሩ እንደሚገኙ ከአቶ ገብሩ ተረድተናል።
የ4መቶ 48 ሺህ ሰዎች የሚኖሩባት አዳማ ከተማ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት የግል ጤና ተቋማት ይገኙባታል።
የጦርነቱን መጀምር ተከትሎ ከወዲሁ የአለም ገበያ በተለይም የነዳጅ ንግድ በርካታ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እያስተናገደ ይገኛል።
ጦርነቱ ከፍ ያለ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ካስከተለባቸው የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል ደሴ አንደኛዋ ምናልባትም ዋነኛዋ ተብላ ልትጠቀስ ትችላለች።
ባጃጆቹ ከያዝነው ሳምንት ጀምሮ በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲያቋርጡ ውሳኔ ተላልፏል።