በድሬደዋ አስተዳደር ከሆስፒታሎች የሚገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከ600 በላይ ሰዎች በአመት የኩላሊት እጥበት እንደሚያስፈልጋቸው አቶ አቤል ተናግረዋል፡፡
ዉሽዉሽ ሻይ ልማት ድርጅት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል አረንጓዴ ሻይ ቅጠል በኪ.ግ በ4.92 ብር እንዲሁም ለውጭ ገበያ ደግሞ በ7.38 ብር ከአርሶ አደሮቹ ላይ ይረከባል።
በአብዛኛው የመንግስት ህክምና ተቋማት እጥረት የተፈጠረበት የማደንዘዣ መድኃኒት ከዛሬ ግንቦት 15 ቀን ጀምሮ በሚገቡት መድኃኒቶች እጥረቱ እንደሚፈታ አቅራቢው ገልጿል
የቤተመንግስቱ አጥር በወቅቱ ባለመታደሱና የውስጥ ቅርሱም ጥበቃ ስለማይደረግለት ለከፋ ጉዳትና ጥፋት እየተዳረገ ይገኛል።
ይህ ፕሮጀክት ቀጣይነት ያለው ፕሮጀክት ስለሆነ አዲስ ገቢ እና ነባር ተማሪዎችን የቃልኪዳን-ቤተሰብ እንዲኖራቸው በማድረግ ከክልሎች ጋር ያለንን ወንድማማችነት ለማጠናከር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ" እንደሚገኙ ተነግረዋል
ባለሙያዎችን ያለማማከር እና ለጥንታዊ የኪነ ህንፃ ውጤቶች ጥበቃ ዋጋ አለመስጠት ያመጣው ውሳኔ ነው። የኪነ ህንፃ አሁን የደረሰበት ዘመን ምንም ዓይነት ገደቦች የሌሉትና ጊዜውን የዋጀ ነው
በአለፉት ዓመታት በባህር ዳር ከተማ ቦታ ከወሰዱ 664 ባለሃብቶች መካከል 142 ብቻ ግንባታቸውን ጨርሰው ወደ ማማረት አንደገቡ ተነገረ፡፡
በመዲናዋ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የእሳት አደጋ ጭማሬ ማሳየቱ ተገልጿል
የምግብ እና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ማህበረሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል
በሰብስቴሽኑ ላይ ብልሽት ሲከሰት የጥገና ቡድኑ ከሻሸመኔ 400 ኪ.ሜ ተጉዞ እስኪደርስ ለቀናት የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ስለሚፈጠር ከፍተኛ የደንበኞችን ቅሬታና ግጭት አስከትሏል